የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ በተገኙበት የነጭ ሪቫን ቀን እየተከበረ ነው

By ዮሐንስ ደርበው

December 01, 2023

 

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት በሀገር አቀፍ ደረጃ በኦሮሚያ ክልል አዘጋጅነት የነጭ ሪቫን ቀን እየተከበረ ነው፡፡

ቀኑ ”መቼም፣ የትም፣ በምንም ሁኔታ ስለ ፆታዊ ጥቃት ዝም አንልም” በሚል መሪ ሐሳብ እየተከበረ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በአከባበሩ ላይ÷ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) እንዲሁም ከክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ የሴቶችና ሕጻናት ዘርፍ አመራር አባላትና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቷ በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት ፆታዊ ጥቃትን መከላከል የሰብአዊ መብት ጉዳይ ነዉ ብለዋል።

ከሰብዓዊ መብቶች ጥሰት አንዱ የሆነውን ፆታዊ ጥቃት መከላከልና ማውገዝ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!