የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ጥላሁን ከበደ በዳሰነች በጎርፍ አደጋ ጉዳት ከደረሰባቸው ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ

By Meseret Awoke

December 02, 2023

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ የተከሰተውን የጎርፍ አደጋ በዘላቂነት ለመፍታት ከአርብቶ አደሩ ጋር ተወያይተዋል፡፡

አቶ ጥላሁን ከበደ ከሌሎች የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ጋር በመሆን በኦሞ ወንዝ ሙላት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎችና አካባቢዎች ዛሬ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በታችኛው ኦሞ ሸለቆ አካባቢ የሚገኘው ዳሰነች ወረዳ በተደጋጋሚ በጎርፍ አደጋ ከሚጠቁ አካባቢዎች አንዱ ነው።

ወረዳውን አቋርጦ የሚያልፈው የኦሞ ወንዝ በአካባቢው የሚገኙ 34 ቀበሌዎች ላይ ጉዳት ማድረሱ ነው የተገለጸው፡፡

በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ምክንያትም በመንግስት ተቋማት እና በሰብሎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ተመላክቷል፡፡

በዚህም በአሁኑ ወቅት በርካታ አርብቶ አደሮች በጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ እንደሚገኙ በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል። አቶ ጥላሁን እና ሌሎች የክልሉ የሥራ ኃላፊዎች በወረዳው በጎርፍ አደጋ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎች ከተመለከቱ በኋላ ከአርብቶ አደሩ ጋር መክረዋል።

ውይይቱም በአካባቢው የሚከሰተውን የጎርፍ አደጋ በዘላቂነት መፍታት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!