የሀገር ውስጥ ዜና

ፀደይ ባንክ በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች የ50 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

By Meseret Awoke

December 02, 2023

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፀደይ ባንክ በሰሜን ጎንደር ዞን እና ዋግ ኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች የሚውል የ50 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል።

በሰሜን ጎንደር ዞን እና ዋግ ኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የተከሰተው ድርቅ በቁም እንስሳትና በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ድጋፉ በአካባቢዎቹ በሰው ሰራሽና ተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች እንደሚዳረስ ነው የተገለጸው፡፡

የተደረገው ድጋፍም በእህት ድርጅቱ የአማራ መልሶ ማቋቋም ልማት ድርጅት (አመልድ) በኩል ለተጎጂዎች እንደሚሰራጭ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር አለማየሁ ዋሴ (ዶ/ር ) ተናግረዋል፡፡

እንደ ፀደይ ባንክ ሁሉ ሌሎች የፋይናንስ ተቋማትም የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት ድጋፍ እንዲያደርጉም ነው ጥሪ ያቀረቡት።

በክልሉ 5 ሚሊየን የሚደርሱ ዜጎች የዕለት ደራሽ እርዳታ ምግብ እንደሚያስፈልጋቸው ተገልጿል፡፡

በትዕግስት ብርሃኔ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!