የሀገር ውስጥ ዜና

የእስር ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ ዜጎች ወደ ሀገር ቤት ተመለሱ

By Mikias Ayele

December 02, 2023

አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በታንዛኒያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ እና የእስር ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ 95 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር ቤት ተመለሱ፡፡

ዜጎቹ ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱም በታንዛኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲና ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ትብብር ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡

በዚህ ሣምንት ብቻ 191 ዜጎች ከእስር ተፈትተው ወደ ሀገር ቤት መመለሳቸውን የኤምባሲው መረጃ አመላክቷል፡፡

በቀጣይም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ዜጎችን ወደ ኢትዮጵያ የመመለስ ሥራ እንደሚከናወን ተመላክቷል፡፡