አዲስ አበባ፣ግንቦት 18፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በአንድነት የምንፈልጋትን ኢትዮጵያ ለመገንባት በዓላማ፣ በሐሳብና በትጋት እንነሣ ሲሉ ጥሪ አቀረቡ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ እንዳስታወቁት÷ ኢትዮጵያውያን ብልጽግና ይመጥናቸዋል፣ ይገባቸዋልም ሲሉ ገልጸዋል።
ሰዎች እንደመሆናችን ያለፍንበትን የታሪክ ውጣ ውረድ በቀላሉ እንረሳለን÷ የአካባቢያችንን፣ የአኗኗራችንን፣ የከተሞቻችንንና እና የሀገራችንን ሁኔታ እኛ ከዚህ የተሻለ አይገባንም፣ ቅብጠት ነው፣ ለድኻ ይሄ መች አነሰው ብለን እንቀጥላለን፣ ኢትዮጵያውያን ግን ብልጽግና ይመጥናቸዋል፣ ይገባቸዋልም ነው ያሉት።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የእኔ አስተዳደርም ለዚህ መሳካት በቁርጠኝነት ይሠራል ብለዋል፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት፣ በቤተ መንግሥቱ ቅጽር ግቢና በአዲስ አበባ እየተለወጡ ያሉ ነገሮች ለራስ ከፍ ያለ ቦታ እንድንሰጥ የሚያስችሉ በመሆናቸው መቀጠል አለባቸው ሲሉ ገልጸዋል።
ከጥቂት ዓመታት በፊት በእነዚህ በሮች ያለፉ ኢትዮጵያውያን በግቢው ሕይወት ለመዝራት የተሠራውን የፈጠራ ችሎታ እና ጉልበት ሳያደንቁ አያልፉም፥ በአንድነት የምንፈልጋትን ኢትዮጵያ ለመገንባት በዓላማ፣ በሐሳብና በትጋት እንነሣ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።