የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ቻም ኡጋላ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዚዳንት ፑቲን አቀረቡ

By ዮሐንስ ደርበው

December 05, 2023

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው የተሾሙት ቻም ኡጋላ ኡሪያት የሹመት ደብዳቤያቸውን ለሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን አቅርበዋል፡፡

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ፕሬዚዳንት ፑቲን ባደረጉት ንግግር÷ ኢትዮጵያና ሩሲያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከመሰረቱ 125 ዓመታት ያስቆጠሩ ወዳጅ ሀገራት መሆናቸውን አስታውሰዋል፡፡

በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሩሲያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት በማድረግ የተለያዩ የትብብር ስምምነቶች መፈረማቸውም ግንኙነቱን ከፍ ወዳለ ደረጃ እንዳሻገረው ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀሏም ግንኙነታቸውን የበለጠ እንደሚያጠናክረው ፕሬዚዳንቱ መናገራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!