አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ክልል የሥራ ዕድል ፈጠራ ምክር ቤት 5ኛ መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ ነው።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ በጉባዔው ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ዘርፎችን ዕድገት ለማፋጠን ሥራ አጥነትን መቀነስ ይገባል ብለዋል።
የወጣቶችን የሥራ ፍላጎት የሚያነሳሱ ለውጥ ተኮር ሥራዎችን መሥራት ከተቻለ ሁለንተናዊ ለውጥ በአጭር ጊዜ ማምጣት እንደሚቻል አብራርተዋል።
የሥራ አጥነት ችግሮችን ከመሰረቱ ለመቅረፍም የባለድርሻ አካላት ተሳትፎና ምክክር ወሳኝ በመሆኑ÷ የሥራ ዕድል ምክር ቤቱን ዐቅም ማሣደግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የክልሉ የሥራ ዕድል ፈጠራ ቢሮ ኃላፊ ሰናይ አኩዎር በበኩላቸው÷ በክልሉ ሥራ አጥነትን ለመቀነስ የሚያስችሉ አበረታች የልማት ሥራዎች መጀመራቸውን ገልፀዋል።
የወጣቶችን ሥራ አጥነት ለመቅረፍም ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን እንዲወጡ መጠየቃቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!