የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ አሻድሊ ሀሰን በዐርባ ምንጭ ከተማ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ

By ዮሐንስ ደርበው

December 05, 2023

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን በዐርባ ምንጭ ከተማ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ ወደ ዐርባ ምንጭ ከተማ ያቀኑት÷ “ከእዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ ሐሳብ በተዘጋጀው 4ኛ ዙር የመንግሥት አመራሮች የዐቅም ግንባታ ስልጠና ላይ ማጠቃለያ ለመስጠት ነው፡፡

ከስልጠናው ማጠቃለያ ጎን ለጎንም በዐርባምንጭ ከተማ የሚገኙ የተፈጥሮ ደን እንዲሁም የዓዞ እርባታ ማዕከልን እና የተለያዩ የልማትና የመስኅብ ሥፍራዎችን ጎብኝተዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!