አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስትሩ ብናልፍ አንዷለም በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኘውን ካርቪኮ ኢትዮጵያ የተሰኘ የስፖርት ትጥቅ ማምረቻ ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝቱ ወቅት እንደተገለጸው÷ ፋብሪካው የስፖርት ትጥቆችን በማምረት ለአውሮፓ ገበያ በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡
እንደ ካርቪኮ ኢትዮጵያ ዓይነት ፋብሪካዎች የውጭ ምንዛሬን በማምጣት ረገድ ሚናቸው የጎላ መሆኑን አቶ ብናልፍ ተናግረዋል፡፡
ኢንዱስትሪዎች ገበያ፣ ካፒታል እና ብቁ የሰው ኃይል እንደሚያስፈልጋቸው ሁሉ ሰላምም መሠረታዊ ጉዳይ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሩ፥ ቀጣናው በሰሜኑ የሀገራችን ጦርነት ከፍተኛ ጉዳት ማስተናገዱንም አስታውሰዋል፡፡
አሁን ያለውን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ማሳሰባቸውን የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!