አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሸዋል ኢድ በዓል አከባበር በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና ባህል ተቋም (ዩኔስኮ) በማይዳሰስ ቅርስነት ተመዝግቧል።
በዚህም የሸዋል ኢድ በዓል ሀገራችን በማይዳሰስ ቅርስነት በዩኔስኮ የተመዘገበ 5ኛ ቅርስ ያደርገዋል።
ኢትዮጵያ ካሏት ደማቅ ማህበራዊ እሴቶች ውስጥ አንዱ የሸዋል ኢድ በዓል አከባበር የአለም ቅርስ ሆኖ መመዝገቡ የቱሪስት ፍሰቱ እንዲጨምር ከማድረጉም ባለፈ የሀገር መልካም ገፅታ በመገንባት ረገድ ፋይዳው የላቀ መሆኑን የሐረሪ ክልል ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።
የሸዋል ኢድ በዓለም ቅርስነት መመዝገቡ የክልሉን የቱሪዝም ማዕከልነት የሚያሳድገው ከመሆኑ ተጨማሪ የህዝብን ተጠቃሚነት ከማሳደግ አንፃር ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተጠቁሟል።
#Ethiopia ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!