የሀገር ውስጥ ዜና

አንጋፋው ጋዜጠኛ አስፋው ገረመው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

By Shambel Mihret

December 06, 2023

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አንጋፋው የኢትዮጵያ ሬዲዮ ጋዜጠኛ አስፋው ገረመው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡

ጋዜጠኛ አስፋው ገረመው ከ30 ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ ሬዲዮ ዜናን ጨምሮ የተለያዩ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀትና በማቅረብ አገልግሏል።

ጋዜጠኛ አስፋው “ይህ የኢትዮጵያ ሬዲዮ ነው” የሚለውን ድምፅ ጨምሮ አሁንም ድረስ አየር ላይ የሚገኙ ስራዎች ያሉት ተወዳጅ ጋዜጠኛ ነበር።

ኢትዮጵያን እንቃኛት፣ ከአድማስ ባሻገር፣ የሬዲዮ መዝናኛ፣ ዜና፣ ኪነ-ጥበባት፣ ቅዳሜ መዝናኛ እና የመሳሰሉ ዝግጅቶች ላይ ደማቅ አሻራውን አሳርፏል።

የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ዛሬ ኅዳር 26 ቀን 2016 ዓ.ም በቀጨኔ መድኃኒዓለም መካነ-መቃብር ከ8 እስከ 9 ሰዓት እንደሚፈጸም ኢቢሲ በዘገባው አስታውሷል።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ለጋዜጠኛ አስፋው ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች መፅናናትን ይመኛል።