አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ማዕከላት ሲሰጥ የነበረው 4ኛው ዙር የመንግሥት አመራሮች የዐቅም ግንባታ ሥልጠና ተጠናቀቀ፡፡
ሥልጠናው “ከዕዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ ሐሳብ በሀገር ዐቀፍ ደረጃ በተለያዩ ማዕከላት ለመንግሥት አመራሮች ሲሰጥ ቆይቷል፡፡
ከሥልጠናው ጎን ለጎንም አመራሮች በተመደቡበት ማዕከል አካባቢ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችንና መስኅቦችን መጎብኘታቸው እንዲሁም የተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ድጋፍ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡
ሥልጠናው ኅብረ- ብሔራዊ አንድነትን፣ እህትማማችነትና ወንድማማችነትን የሚያጠናክር መሆኑን ሰልጣኞች ተናግረዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!