አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ባንክ ሥራ አስፈፃሚ አባላት ከነገ ጀምሮ በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ተገለጸ፡፡
የዓለም ባንክ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አና ቤርዴ እና የባንኩ የደቡብ እና ምሥራቅ አፍሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ቪክቶሪያ ክዋክዋ በጉብኝቱ እንደሚሳተፉ የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡
የጉብኝቱ ዓላማም÷ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በዓለም ባንክ መካከል ያለውን ትብብር በይልጥ ለማጠናከር መሆኑ ተገልጿል፡፡
በጉብኝታቸውም ከኢትዮጵያ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች እና ከልማት አጋሮች ጋር እንደሚመክሩ ይጠበቃል ተብሏል፡፡
ሥራ አስፈጻሚዎቹ በኢትዮጵያ ቆይታቸው የከተማ ሴፍቲ ኔት እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ፕሮጄክቶችን እንደሚጎበኙም ተመላክቷል፡፡