የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ 627 ባለሙያዎችን አስመረቀ

By Shambel Mihret

December 09, 2023

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ 627 የአቪዬሽን ባለሙያዎችን አስመርቋል፡፡

ከተመራቂዎች መካከል 88 አብራሪዎች፣ 125 የአውሮፕላን ቴክኒሻኖች፣ 150 የበረራ መስተንግዶ ባለሙያዎች እንዲሁም 264 የትኬት ሽያጭ እና የደንበኛ አገልግሎት ባለሙያዎች እንደሚገኙበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ መረጃ ያመላክታል፡፡