የሀገር ውስጥ ዜና

በክልሉ በ3 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር የመንገዶች ግንባታና ጥገና እንደሚከናወን ተገለጸ

By Mikias Ayele

December 10, 2023

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2016 የጀት ዓመት በ3 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጪ የአዳዲስ መንገዶች ግንባታና ጥገና እንደሚያከናወን የአማራ ክልል መንገድ ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው የ2016 በጀት ዓመት ዕቅዱን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት በጎንደር ከተማ ውይይት አካሂዷል፡፡

የቢሮው ኃላፊ ጋሻው አወቀ (ዶ/ር) በውይይቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ከታኅሣስ 1 ቀን ጀምሮ በሚከናወኑ የበጀት በበጀቱ ሥራዎች 118 አዲስ የመንገድ ፕሮጀክቶች ግንባታ እና ጥገና ይከናወናል ብለዋል፡፡

ከዚህ ውስጥም ከ12 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ ያህሉ የመንገድ ጥገና መሆኑን ጠቁመው÷ 92 ድልድዮች እንደሚገነቡም አንስተዋል፡፡

የበጀት ዓመቱን ዕቅዶች ለማሳካትም 2 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ከክልሉ እና ከፌዴራል መንግሥት ተመደቧል ብለዋል፡፡

እንዲሁም 800 ሚሊየን ብር ገደማ በኅብረተሰቡ ተሳትፎ እንደሚሸፈን አመላክተዋል፡፡