የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ምስጋኑ ከኳታር ልማት ፈንድ ዋና ዳይሬክተር ጋር መከሩ

By Mikias Ayele

December 11, 2023

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከኳታር ልማት ፈንድ ዋና ዳይሬክተር ካሊፋ ቢን ጃዚም አል ኩዋሪ ጋር ተወያይተዋል፡፡

አምባሳደር ምስጋኑ በዚህ ወቅት ÷ ኳታር ለኢትዮጵያ በኢኮኖሚያዊ ትብብር ተመራጭ አጋር መሆኗን ገልፀዋል፡፡

በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ፖለቲካዊ አጋርነት ወደ ኢኮኖሚያዊ አጋርነት በመቀየር የሁለቱን ሀገራት ህዝቦች ተጠቃሚ ማደረግ እንደሚገባም ነው የተናገሩት፡፡

በተጨማሪም በኢትዮጵያ እና ኳታር መካከል ያለውን ኢኮኖሚያው ትብብር የበለጠ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡

በውይይቱ ሁለቱ ወገኖች የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማሳደግ፣ ትብብራቸውን ለማስፋትና አዳዲስ የትብብር መስኮችን ለማጠናከር መስማማታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚነስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡