የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ለኬንያውያን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

By Shambel Mihret

December 12, 2023

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ለኬንያውያን 60ኛ አመት የነጻነት ቀን በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ፕሬዚዳንቷ በ60ኛው የኬንያ ነጻነት ቀን ላይ በኬንያ ናይሮቢ ተገኝተው በኢትዮጵያ ህዝብ ስም መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በመልዕክታቸው÷ ለኬንያውያን ያላቸውን ክብር ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያውያንን ወክለው መገኘታቸውን ገልጸው “እንኳን ለነጻነት ቀን በዓል ሁላችሁም አደረሳችሁ” ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ለኬንያውያን ስኬት ፣ ብልጽግና እና ደስታ መልካም  ምኞታቸውንም በመድረኩ ገልጸዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ በ60ኛው የኬንያ ነጻነት ቀን (ጃምሁሪ) በዓል ላይ ለመታደም ትናንት ወደ ናይሮቢ ማቅናታቸው ይታወቃል፡፡