የሀገር ውስጥ ዜና

በትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ሕይወት አለፈ

By ዮሐንስ ደርበው

December 13, 2023

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በስልጤ ዞን ሁልባራግ ወረዳ ወራበት ሻማ ቀበሌ በሚገኝ ወንዝ ድልድይ አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡

አደጋው የደረሰው ዛሬ ረፋድ ላይ ከወላይታ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ወደ ወራቤ በመጓዝ ላይ ከነበሩ ሁለት ሞተረኞች ጋር በመጋጨቱ ነው፡፡

ሞተረኞቹ ወደ ወራቤ ሆስፒታል ተወስደው የሕክምና ዕርዳታ እየተደረገላቸው ሳለ ሕይወታቸው አልፏል ተብሏል፡፡

የህዝብ መመላለሻ ተሽከርካሪውን በመተው አሽከርካሪው ለጊዜው መሰወሩን የወራቤ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!