የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያን ግብርና ምርቶች የሚያስተዋውቅ መካነ ርዕይ በዶሃ ከተማ ተከፈተ

By Mikias Ayele

December 13, 2023

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን ግብርና ምርቶች የሚያስተዋውቅ መካነ ርዕይ በኳታር ዶሃ ተከፍቷል፡፡

መካነ ርዕዩ በኳታር እየተካሄደ በሚገኘው ዓለም አቀፍ የአትክልት እና ፍራፍሬ አውደ ርዕይ ላይ የተከፈተ ሲሆን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በይፋ መርቀው ከፍተውታል፡፡

በሥነ-ስርዓቱ ላይ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ (ዶር)፣ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ እንዲሁም በዶሃ የሚገኙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት መገኘታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡