የሀገር ውስጥ ዜና

“የመደመር ጉዞ” የፓናል ውይይት በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው

By Feven Bishaw

December 14, 2023

 

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) “የመደመር ጉዞ” የፓናል ውይይት “የመደመር ትሩፋቶች ለተሻለ ነገ” በሚል መሪ ሀሳብ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነዉ ።

በውይይቱ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር)ን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስተር ተስፋዬ በልጅጌ፣ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አመራሮች እና ሌሎችም አካላት ተገኝተዋል።

የመደመር ጉዞ የፓናል ውይይት መድረኮች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “መደመር”፣ “የመደመር መንገድ” እና “የመደመር ትውልድ“ በሚሉ ርዕሶች ለንባብ ያበቋቸውን መጽሃፍት መሰረት ያደረጉ ናቸው ተብሏል።

በርዕሰ ጉዳዩ ላይ የውይይት መነሻ ሃሳቦች እየቀረቡ ሲሆን÷ ሰፊ ውይይት ይደረግባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።

በምንተስኖት ሙሉጌታ