የሀገር ውስጥ ዜና

በአዲስ አበባ ለኮሮና ቫይረስ ሕሙማን ሕክምና መስጫ የሚውል ፊልድ ሆስፒታል ተገነባ

By Tibebu Kebede

May 27, 2020

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ለበርካታ የኮሮና ቫይረስ ሕሙማን ሕክምና መስጫ የሚውል ‘አዲስ አበባ ኮቪድ-19 ፊልድ ሆስፒታል’ ተገነባ።

በቅርቡ ሥራ የሚጀምረውን ሆስፒታል የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰና የዓለም የምግብ መርኃ ግብር ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቤስሌይ መርቀው ከፍተውታል።