አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከአለም አቀፍ ስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) ዋና ዳይሬክተር ኤሚ ፖፕ ጋር ተወያይተዋል፡፡
አቶ ደመቀ መኮንን በጄኔቫ እየተካሄደ ካለው ዓለም አቀፍ የስደተኞች ፎረም ጎን ለጎን ነው ውይይቱን ያካሄዱት፡፡
በውይይቱ አቶ ደመቀ መኮንን የህገ ወጥ ስደት ተግዳሮቶችን ለመፍታት ስደትን ከልማት ጋር ማስተሳሰር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሯ በበኩላቸው የጋራ ፍላጎቶችን ለመፍታት ተቋማቸው ትብብሩን የበለጠ ለማጠናከር ቁርጠኛ እንደሆነ አረጋግጠዋል፡፡
እንዲሁም አይኦኤም ስደትን ከዘላቂ ልማት ጋር ለማስተሳሰር እና አጋርነትን ለማጠናከር መስማማቱንም ገልጸዋል፡፡