የሀገር ውስጥ ዜና

የአፍሪካ ሀገራት የአየር ኃይል አዛዦችና ወታደራዊ አታሼዎች የአንድነት ፓርክን ጎበኙ

By Feven Bishaw

December 15, 2023

 

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የአየር ኃይል አዛዦች እና ወታደራዊ አታሼዎች የአንድነት ፓርክን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ የበርካታ የአፍሪካ ሀገራት የአየር ኃይል አዛዦችና ወታደራዊ አታሼዎች እየተሳተፉ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

የአየር ኃይል አዛዦችና ወታደራዊ አታሼዎች በትናንናው ዕለት የኢትዮጵያ አየር ኃይል ያስገነባቸው የውጊያ መሠረተ-ልማቶች እንዲሁም የትጥቅ አቅምን ለማሳደግ የተከናወኑ የለውጥ ስራዎችን ጎብኝተዋል።

በወቅቱም አየር ኃይሉ እያስመዘገባቸው ያሉ ለውጦችን፣ የደረሰበት ደረጃና ስለገነባው አቅም ገለጻ ተደርጎላቸዋል።

ተሳታፊዎቹ በዛሬው ዕለት ሌሎች የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው እንደሚጎበኙ ይጠበቃል።