የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ አየር ኃይል የሠው አልባ የአየር ምድብን መርቀው ከፈቱ

By Tamrat Bishaw

December 16, 2023

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣስ 6 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ አየር ኃይል የሠው አልባ የአየር ምድብን መርቀው ከፈቱ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በከሠዓት መርሐ ግብር የኢትዮጵያ አየር ኃይል ለመጀመሪያ ጊዜ ያሰለጠናቸውን እጩ መኮንኖች፣ የአውሮፕላን ጥገና ሙያተኞችን እና ፓይለቶችን እንደሚያስመርቁ ይጠበቃል።

88ኛው የኢትዮጵያ አየር ሃይል የምስረታ በዓል በልዩ ልዩ ዝግጅቶቾ እየተከበረ መሆኑን የመከላከያ ሰራዊት ገጽ መረጃ ያመላክታል።