ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ኢትዮጵያ መድን ድል ቀንቷቸዋል

By Shambel Mihret

December 16, 2023

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 8ኛ ሳምንት በዛሬው እለት ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ መጀመሪያ 9 ሰዓት ላይ በተካሄደ ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኢትዮጵያ ቡናን 2 ለ 1 አሸንፏል።

አዲስ ግደይ እና ባሲሩ ኡመር ለኢዮጵያ ንግድ ባንክ የማሸነፊያ ጎሎቹን ሲያስቆጥሩ ዴሬክ ካኮዛ ደግሞ የኢትዮጵያ ቡናን ጎል አስቆጥሯል።

ማምሻውን 12 ሰዓት ላይ በተካሄደ ሁለተኛው ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን ድል ቀንቶታል፡፡

በዚህም ከሀምበሪቾ ዱራሜ ጋር የተጫወተው ኢትዮጵያ መድን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ቹኩዌሜኬ ጎድሰንና ያሬድ ዳርዛ ለኢትዮጵያ መድን የማሸነፊያ ግቦችን አስቆጥረዋል።