አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሕንድ በተካሄደ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡
ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሱቱሜ አሰፋ በሕንድ ኮልካታ ከተማ የተካሄደውን የ25 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በቀዳሚነት አጠናቅቃለች፡፡
አትሌቷ ርቀቱን 1ሰዓት 18 ደቂቃ ከ47 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ቀዳሚ የሆነቸው ፡፡
በውድድሩ አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው ሁለተኛ ደረጃ መያዟን ከታታ ስቲል ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በተጨማሪም በተመሳሳይ የሩጫ ውድድር በወንዶች ዘርፍ አትሌት ተስፋዬ ደመቀ ሦስተኛ በመውጣት አጠናቅቋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!