የሀገር ውስጥ ዜና

ለአትሌት አበበ ቢቂላ መታሰቢያ የግማሽ ማራቶን ውድድር በጃፓን ተካሄደ

By Meseret Awoke

December 17, 2023

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለጀግናው አትሌት አበበ ቢቂላ መታሰቢያ የግማሽ ማራቶን ውድድር በጃፖን ካሳማ ከተማ ተካሂዷል፡፡

በጃፓን ኢባራኪ ግዛት ካሳማ ከተማ በተካሄደው የጀግናው አትሌት አበበ ቢቂላ መታሰቢያ ግማሽ ማራቶን ውድድር ላይ ከ1 ሺህ 600 በላይ ሯጮች ተሳትፈዋል።

የግማሽ ማራቶን ውድድሩን በጃፓን የኢፌዲሪ ባለሙሉስልጣን አምባሳደርና ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዳባ ደበሌ አስጀምረዋል፡፡

አምባሳደሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት ፥ መሰል ወድድሮች ረጅም ዘመናት ያስቆጠረውን የሁለቱን ሀገራት ዘርፈ ብዙ ግንኙነቱ ይበልጥ አጠናክሮና አስተሳስሮ ለማስቀጠል ሚናው የጎላ ነው።

የጃፖን መንግስት ይህን ውድድር በማዘጋጀቱና የጀግናው አትሌት አበበ ቢቂላ መታሰቢያ በማድረጉ ምስጋና አቅርበዋል።

የካሳማ ከተማ ከንቲባ ሺንጁ ያማጉቺ በበኩላቸው ፥ ከተማው ከኤምባሲው ጋር እየሰራ ያለውን ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራቸውን በጃፓን የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡፡

በቀጣይም ከከተማዋ አስተዳደር የተውጣጣ ልዑክን በመምራት ኢትዮጵያን እንደሚጎበኙና ከኢትዮጵያ ከተሞች ጋር ትስስር በመፍጠር በትብብር መስራት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!