አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል ለልማታዊ ሴፍትኔት የተመደበው በጀት ለታለመለት ዓላማ አለመዋሉን በመስክ ምልከታ ማረጋገጡን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ፣ መሠረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡
በከተሞች የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በዓለም ባንክ እየተደረገ ያለው ድጋፍ በአግባቡ ሥራ ላይ ባለመዋሉ በልማታዊ ሴፍትኔት የታቀፉ ተጠቃሚዎችን ማግኘት እንዳልተቻለም ነው የቋሚ ኮሚቴው ቡድን መሪ ገነት ከተማ የተናገሩት፡፡
የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ባንቻየሁ ድንገታ በበኩላቸው÷ ቋሚ ኮሚቴው ያቀረበው የመስክ ግኝት ለቀጣይ ክትትልና ቁጥጥር ሥራ ጠቃሚ ግብዓት ይሆናል ማለታቸውን ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡
በቋሚ ኮሚቴው የቀረበላቸውን አቅጣጫ በቀጣይ የዕቅዳቸው አካል አድርገው የተለዩትን ክፍተቶች ለማስተካከል እንደሚሠራ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ ቴንኩዌይ ጆክ ጠቁመዋል፡፡
ለክልሉ የሚያስፈልጉትን የድጋፍና ክትትል ሥራዎች ለይቶ በመውሰድ ከሚመለከታቸው የፌዴራል አስፈፃሚ አካላት ጋር በመነጋገር በክልሉ የሚስተዋሉ ችግሮች እንዲቀረፉ ቋሚ ከሚቴው በትኩረት እንደሚሠራም ወ/ሮ ገነት አመላክተዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!