አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የሚገኘው የሩሲያ የሣይንስና የባሕል ማዕከል የመሬት ጥናት (ጂኦሎጂ) ትምህርት ክፍል መክፈቱን አስታውቋል፡፡
በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተረኺን የትምህርት ክፍሉን መከፈት በሚያስተዋውቀው ሥነ-ሥርዓት ላይ እንዳሉት÷ ኢትዮጵያና ሩሲያ ከምዕተ- ዓመታት በላይ የዘለቀውን ግንኙነታቸውን በዘርፈ ብዙ የትብብር መስኮች እያጠናከሩ ነው፡፡
የሩሲያ የሣይንስና የባሕል ማዕከልም ከዚህ በፊት ሲሰጥ በነበረው የቋንቋ ትምህርት ላይ የማስፋፊያ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን አስታውሰው÷ በዛሬው ዕለት ይፋ የተደረገው የሥነ-መሬት ጥናት ትምህርት ክፍል መከፈት አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
ማዕከሉ የሩሲያ ቋንቋና የሥነ- ጥበብ ትምህርት ለኢትዮጵያውያን እየሰጠ መሆኑን ጠቁመው÷ በዚህም የሀገራቱን የባሕል ብሎም የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት በማጠናከር ረገድ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
አዲስ የተከፈተው የመሬት ጥናት ክፍልም ሀገራቸው በዘርፉ ያካበተችውን ልምድ ለኢትዮጵያ ለማካፈል ያላትን ፍላጎት እንደሚያሳይ ነው በአጽንኦት የገለጹት፡፡
ትውልዱ ኢትዮጵያ ከመሬት በታች ያላትን ዕምቅ ሐብት መለየት እና ልማት ላይ ማዋል እንዲችልም ያግዛል ነው ያሉት፡፡
የማዕከሉ መምህርት አልማዝ ገብረ መስቀል በበኩላቸው÷ የትምህርት ክፍሎቹን በማስተማሪያ ቁሳቁስ፣ በቴክኖሎጂ ግብዓቶች እና በሰው ኃይል የማጠናከር ተግባራት መከናወናቸውን ጠቅሰዋል፡፡
ማዕከሉ ከሚሰጣቸው ትምህርቶች በተጓዳኝ ለሚያስተምራቸው ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በሩሲያ ተቋማት ነጻ የትምህርት ዕድል በማመቻቸት ላይ እንዲሚገኝም ነው ያመላከቱት፡፡
በወንደሰን አረጋኸኝ
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!