የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ አሮጌ ተሸከርካሪዎች ሊታገዱ ነው በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ሃሰተኛ ናቸው ተባለ

By Meseret Awoke

December 18, 2023

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አሮጌ ተሽከርካሪዎች ሊታገዱ ነው እየተባለ በማህበራዊ ትስስር ገጾች የሚሰራጩ መረጃዎች ሀሰተኛ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ገለጸ፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዲዳ ድሪባ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ ተሽከርካሪዎች የሚያወጡት በካይ ጋዞች (ጭሶች) አካባቢን እንዳይበክሉ ተቋሙ የልኬት ቁጥጥር ያደርጋል ብለዋል፡፡

በዚያ መሰረትም ማስተካከያ እንዲያደርጉ ይደረጋልም ነው ያሉት።

ለዚህ የቁጥጥር ስራ እንዲያመች ደግሞ ከተሽከርካሪዎች የሚወጡ በካይ ጋዞችን መቆጣጠር የሚያስችል መመሪያ እየተዘጋጀ እንደሆነ ጠቁመዋል።

መመሪያው አሮጌ ተሽከርካሪዎችን ከመስመር ለማስወጣት ሳይሆን በካይ ጋዝ የሚያወጡ ተሽከርካሪዎችን በመቆጣጠር ማስተካከያ እንዲያደርጉ የሚያስችል እንደሆነም ነው ስራ አስኪያጁ የጠቆሙት።

በዚህም ከዓመታዊ የቦሎ እድሳት ጋር የተሽከርካሪው የበካይ ጋዝ ምርመራ የማረጋገጫ ስራ አንዱ መሆኑን ተናረዋል፡፡

በታሪክ አዱኛ

#Ethiopia #AddisAbeba

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!