የሀገር ውስጥ ዜና

1 ነጥብ 6 ሚሊየን ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ ስንዴ ተሸፈነ

By Meseret Awoke

December 18, 2023

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በመላው ኢትዮጵያ 1 ነጥብ 6 ሚሊየን ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ ስንዴ መሸፈኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነትና የኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ ከበደ ላቀው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማትን አስመልክቶ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ በበጀት ዓመቱ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት 3 ሚሊየን ሄክታር መሬትን በዘር ይሸፈናል።

ዕቅዱን ለማሳካትም በስፋት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

ከታቀደው 3 ሚሊየን ሄክታር መሬት ውስጥም እስካሁን 1 ነጥብ 6 ሚሊየን ሄክታር በዘር ሊሸፈን መቻሉን ገልጸዋል።

በተጨማሪም 2 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር መሬት መታረሱንም አቶ ከበደ ተናግረዋል፡፡

በዘንድሮው የበጋ ስንዴ ከሚለማው መሬት 117 ሚሊየን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅም ነው ያነሱት፡፡

በመሳፍንት እያዩ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!