የሀገር ውስጥ ዜና

ቦርዱ  ለትንሳኤ ሰብዓ እንደርታ ፓርቲ እና ለየዎላይታ ሕዝቦች ነጻነት ንቅናቄ ፓርቲ እውቅና ሰጠ

By Shambel Mihret

December 18, 2023

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለትንሳኤ ሰብዓ እንደርታ ፓርቲ  እና ለየዎላይታ ሕዝቦች ነጻነት ንቅናቄ ፓርቲ እውቅና መስጠቱን አስታውቋል፡፡

ቦርዱ በአዋጁ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለትንሳኤ ሰብዓ እንደርታ ፓርቲ ሕጋዊ የክልል ፖለቲካ ፓርቲነት ማረጋገጫ የምሥክር ወረቀት መስጠቱን ገልጿል፡፡

እንዲሁም የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለየዎላይታ ሕዝቦች ነጻነት ንቅናቄ ፓርቲ ሕጋዊ የሃገር አቀፍ ፖለቲካ ፓርቲነት ማረጋገጫ የምሥክር ወረቀት መስጠቱን ከቦርዱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡