የሀገር ውስጥ ዜና

ም/ቤቱ ነገ በሚያካሄደው መደበኛ ስብሰባ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢን ጨምሮ የተለያዩ ሹመቶችን ያጸድቃል

By Melaku Gedif

December 18, 2023

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ነገ በሚያካሄደው 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ስብሰባ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢን ጨምሮ የተለያዩ ሹመቶችን መርምሮ ያጸድቃል፡፡

ምክር ቤቱ በ9ኛ መደበኛ ስብሰባው በቅድሚያ የ8ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባዔን በማጽደቅ የዕለቱን ስብሰባ እንደሚጀምር ተገልጿል፡፡

በዕለቱ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢን ጨምሮ የተለያዩ ሹመቶችን መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡