የሀገር ውስጥ ዜና

በእስያ፣ አውስትራሊያና ኒውዚላንድ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር የፊታችን እሁድ ምክክር ይደረጋል

By ዮሐንስ ደርበው

December 19, 2023

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በእስያ፣ አውስትራሊያ እና ኒውዚላንድ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ታኅሣስ 14 ቀን 2016 ዓ.ም ምክክር እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡

ምክክሩ የሚካሄደው በበይነ-መረብ ሲሆን÷ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 4፡00 (በአካባቢዎቹ አቆጣጠር 10 ኤ ኤም ወይም አት ጂ ኤም ቲ ፕላስ 3) መሆኑ ተገልጿል፡፡

በስብሰባው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉም በዚህ ሊንክ https://forms.gle/CsNpWm7pLm4tjdoYA እንዲመዘገቡ ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ምዝገባውን ላከናወኑ አካላትም በኢሜይል አድራሻቸው አማካኝነት የመሰብሰቢያ ሊንኩ እንደሚልክ ተጠቅሷል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!