ምክር ቤቱ አቶ ጌትነት ታደሰን የኢቢሲ ዋና ስራ አስፈጻሚ አድርጎ ሾመ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው እለት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ አቶ ጌትነት ታደሰን የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ዋና ስራ አስፈጻሚ አድርጎ ሾሟል፡፡
በምክር ቤቱ የኢቢሲ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው የተሾሙት አቶ ጌትነት ታደሰ በሚዲያው ዘርፍ ከፍተኛ የሆነ ሙያዊ ልምድ ያላቸውና ውጤታማ አመራር መሆናቸው ተገልጿል፡፡
አቶ ጌትነት ታደሰ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል።
በተጨማሪም ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው አቶ መሳፍንት ተፈራን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ አድርጎ ሾሟል፡፡
እንዲሁም ምክር ቤቱ በ9ኛ መደበኛ ስብሰባው የ8ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባዔንም አጽድቋል፡፡
በየሻምበል ምሕረት