የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሲቲ ግሩፕ ጋር የ450 ሚሊየን ዶላር የብድር ሥምምነት ተፈራረመ

By Meseret Awoke

December 19, 2023

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣስ 9 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሲቲ ግሩፕ ጋር የ450 ሚሊየን ዶላር የብድር ሥምምነት ተፈራረመ

ገንዘቡ ለአምስት አዳዲስ አውሮፕላኖች መግዣ የሚውል መሆኑን የአየር መንገዱ መረጃ ያመለክታል።

ከሚገዙት አውሮፕላኖች ውስጥ ሶስቱ ቦይንግ 737 -8 እና ሁለት ቦይንግ 777 ኤፍ የጭነት አውሮፕላኖች ናቸው።

የአምስቱ አውሮፕላኖች ግዢ የአየር መንገዱን የአውሮፕላን ቁጥር ወደ 150 የሚያሳድገው ይሆናል።

የብድር ሥምምነቱ አየር መንገዱ የሚሰጠውን አገልግሎት ለማስፋት እና በዘርፉ ለመድረስ ያለመውን የእድገት ዕቅዱን ለማሳካት እንደሚያግዘው ታምኖበታል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በፈረንጆቹ 2035 የአውሮፕላኖቹን ቁጥር ከ270 በላይ ለማድረስ ዕቅድ ይዞ እየሰራ ነው።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!