የሀገር ውስጥ ዜና

የአፍሪካ ሀገራት የኤሌክትሮኒክ አስተዳደርና የዲጂታላይዜሽን አገልግሎት ምክክር በሩሲያ እየተካሄደ ነው

By Meseret Awoke

December 19, 2023

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ሀገራት የኤሌክትሮኒክ አስተዳደርና የዲጂታላይዜሽን ምክክር መድረክ በሩሲያ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በሩሲያ ሞስኮ እየተካሄደ በሚገኘው መድረክ የአፍሪካ ሀገራት ቴክኖሎጂን በመጠቀም በሀገራቸው የሚካሄደውን የኢኮኖሚ ስርዓት ለማዘመን የሄዱበትን የስኬት ጉዞና ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ ለሚደረጉ የቴክኖሎጂ ሽግግሮች ተሞክሮ ይቀርብበታል።

ኢትዮጵያን ወክለው በመድረኩ እየተሳተፉ የሚገኙት የአብርሆት ቤተ-መጽሐፍት ዋና ዳይሬክተር ውባየሁ ማሞ (ኢ/ር) ኢትዮጵያ ያላትን ተሞክሮ በመድረኩ አቅርበዋል።

በዚህም የኢትዮጵያን የዲጂታል መታወቂያ አሰጣጥ፣ የኤሌክትሮኒክ ግብይቶችንና ኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባት የምታደርገውን ጥረት በተሞክሮነት አቅርበዋል።

በጉባዔው የአፍሪካ ሀገራት ከሩሲያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ተሞክሮዎችን በመውሰድ አዳዲስ የቴክኖሎጂ አሰራሮችን ተግባራዊ ያደርጉበታል ተብሎ ይጠበቃል።

በመድረኩ 37 የአፍሪካ ሀገራት ተሳትፎ እያደረጉ መሆኑ ታውቋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!