የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ እና ኔዘርላንድስ የ45 ሚሊየን ዩሮ የእርዳታ ሥምምነት ተፈራረሙ

By Feven Bishaw

December 19, 2023

 

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣስ 9 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ኔዘርላንድስ የ45 ሚሊየን ዩሮ የእርዳታ ሥምምነት ተፈራረሙ።

ሥምምነቱ በኢትዮጵያ የተፋሰስ አስተዳደርን ለመደገፍ ለሚውለው ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ እንደሚውል የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

ፕሮጀክቱ በዓባይ፣ አዋሽ፣ በስምጥ ሸለቆ፣ በኦሞ ጊቤ እና ተከዜ ወንዞች አካባቢ ያለውን የተቀናጀ የውሃ ሃብት አስተዳደርን ለማዘመን ያስችላል ነው የተባለው።