አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአቶ አባተ አበበ ግድያ ሲፈለግ የነበረው አቶ ተስፋዬ ሆርዶፋን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
አቶ አባተ አበበ የተባሉ ግለሰብ ታህሳስ 7 ቀን 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ ቦሌ ኤድናሞል አካባቢ ዝቅ ብሎ በሚገኝ ምሽት ክለብ በጥይት ተመትተው መገደላቸው ይታወሳል።
የአዲስ አበባ ፖሊስም ይህን መነሻ በማድረግ የምርመራና የክትትል ስራውን በማከናወን በግድያ ወንጀሉ ሲፈለጉ የነበሩትን አቶ ተስፋዬ ሆርዶፋ በቁጥጥር አውሏቸዋል።
ከጉዳዩ ጋር በተያያዘም ፖሊስ በቀጣይ የምርመራውን ውጤት ለህብረተሰቡ የሚገልጽ መሆኑን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡