የሀገር ውስጥ ዜና

በአማራ ክልል የተገኘውን አንጻራዊ ሰላም ለማጽናት ተከታታይ ምክክር ያስፈልጋል ተባለ

By ዮሐንስ ደርበው

December 20, 2023

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አሁን የተገኘውን አንጻራዊ ሰላም ለማጽናት የሚያስችል ተከታታይ ምክክር እንደሚያስፈልግ የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ አስገነዘቡ፡፡

የክልሉ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በወቅታዊ እና መደበኛ ሥራዎች ዙሪያ ውይይት እያደረጉ ነው።

ርዕሰ መሥተዳድሩ በውይይቱ ላይ ባደረጉት ንግግርም÷ በቀውስ ውስጥም ሆነን መደበኛ ሥራዎችን ለማስቀጠል የሄድንበት ርቀት አበረታች ነበር ብለዋል።

ከነባራዊ ሃቅ የራቁ የግጭት እና ጦርነት መረጃዎች በሚናፈሱበት ክልል የኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ምክክሮችን ማካሄዳችን የበርካቶችን አስተሳሰብ ቀይሯልም ነው ያሉት፡፡

አሁን የተገኘውን አንጻራዊ ሰላም ለማጽናት የሚያስችል ተከታታይ ምክክር እንደሚያስፈልግም በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

በተለይም የመንግሥት ሠራተኛውን ከየተቋሙ ተልዕኮ ጋር አገናኝቶ አገልጋይነቱን እና ኃላፊነቱን እንዲወጣ ማድረግ ያስፈልጋል ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

የውይይቱ ዓላማም÷ ነባራዊ ሃቁን ማስረዳት፣ የጋራ መግባባት መፍጠር እና ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማስገባት መሆኑን አብራርተዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!