የሀገር ውስጥ ዜና

የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር አባላት የዓድዋ ሙዚየምን ጎበኙ

By Shambel Mihret

December 20, 2023

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር አባላት የዓድዋ ሙዚየምን ጎብኝተዋል፡፡

ሙዚየሙ የዓድዋ ድል ጽንስ ማዕከል በሆነችው አዲስ አበባ ከተማ ታሪኩን የሚዘክሩ ሁነቶችንና እውነቶችን አካትቶ እየተገነባ የሚገኝ ፕሮጀክት ነው፡፡

በጉብኝቱ ላይ የተሳተፉት የማህበሩ አባላት ኢትዮጵያውያን በአንድነትና በአርበኝነት ተጋድሎ በደማቸው የኢትዮጵያን ነጻነት ያጸኑበት የጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ትግል ቀንዲል ትውልድ ሊማርበት እንደሚገባ ገልጸዋል።

ለዚህም የሙዚየሙ መገንባት ሌላ ዓድዋ፤ ሌላ ተጨማሪ ድል ነው ማለታቸውን የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡