አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ራስ ገዝ የሆነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመንግስት የተመደቡ የ2016 ተማሪዎችንና በግላቸው ከፍለው መማር የሚችሉ ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው።
ዩኒቨርሲቲው የዘንድሮ ተማሪዎችን “ፍሬሸር ዊክ” በሚል መሪ ሃሳብ ነው አዲስ ተማሪዎችን መቀበል የጀመረው፡፡
በዛሬው እለት ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የመጡ የመጀመሪያ አመት ተማሪዎች በግቢው ስለሚኖራቸው ቆይታ በተለይም ማድረግ ስለሚገባቸውና ከሌሎች ተማሪዎች ጋር ስለሚኖራቸው መስተጋብር እንዲሁም ስለግቢው ሕገደንብ ማብራሪያ ሰጥቷል።
የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር)÷ ተማሪዎቹ አንጋፋ ወደ ሆነው ዩኒቨርሲቲ ሲቀላቀሉ ኃላፊነታቸው ከፍ ያለ መሆኑን ልትረዱ ይገባል ብለዋል።
ተማሪዎች በቆይታቸው የሚትፈልጉትን ዕውቀት፣ ክህሎትና መልካም ስብዕና ገንብተው ለሀገር የሚጠቅሙ እንዲሆኑ ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ሀላፊነቱን እንደሚወጣም አረጋግጠዋል።
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ላለፉት 73 አመታት ለሀገር የሚጠቅሙ መሪዎች፣ ምሁራንና በልዩ ልዩ መስኮች ብቁ የሆኑ ዜጎችን ሲያፈራ ቆይቷልም ብለዋል፡፡
በዓለምሰገድ አሳዬ