አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 5 ወራት የግብይት ሰንሰለቱ ላይ እንቅፋት በመፍጠር የዋጋ ንረት እንዲባባስ ያደረጉ 790 ሕገ- ወጥ ደላላዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱ ተገለፀ፡፡
እየተስተዋለ ላለው የዋጋ ንረት የግብይት ሰንሰለቱ መርዘም፣የደላላዎች ጣልቃ ገብነት እና አላስፈላጊ ኬላዎች ተጠቃሽ መንስኤዎች መሆናቸውን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ሚኒስቴሩ እነዚህን ችግሮች በመፍታት የዋጋ ንረቱን ለማርገብ በርካታ ስራዎችን እየሰራ ሲሆን ÷በግብርና ምርት፣ በአትክልትና ፍራፍሬ፣ በቁም እንስሳት እና በሰብል ምርቶች ግብይት ውስጥ የነበሩ ደላላዎችን ፈቃድ በመሰረዝ ከግብይት ሒደቱ እንዲወጡ አድርጓል፡፡
ባለፉት 5 ወራት በተደረገ ክትትልም እንደ ሀገር በግብይት ሒደቱ ውስጥ ተሳታፊ ሆነው በተገኙ 790 ሕገ-ወጥ ደላላዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱ ተገልጿል፡፡
በቀጣይ የደላላን ጣልቃ ገብነት በዘላቂነት እልባት ለመስጠት የሚያስችል መመሪያ እየተዘጋጀ እንደሆነም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!