የሀገር ውስጥ ዜና

ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ የሚቀርቡ የሰላም አማራጮችን በአግባቡ መጠቀም ይገባል –  ምሁራን

By Shambel Mihret

December 21, 2023

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ የሚቀርቡ የሰላም አማራጮችን በአግባቡ መጠቀም ይገባል ሲሉ ምሁራን ገለጹ፡፡

የሰላም ግንባታና ግጭት አፈታት ምሁር ገለታ ሴኔሶ ዶ/ር) እንደገለጹት ÷ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ተቀራርቦ ከመነጋገር ውጭ ምንም አማራጭ የለም፡፡

በሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ አቶ በፍቃዱ ዳባ በበኩላቸው ÷ በመንግስት የሚቀርቡ የሰላም አማራጮች ኢትዮጵያ ለገጠማት የሰላም እጦት መፍትሄ የሚሆኑ ናቸው ብለዋል፡፡

ህብረተሰቡም የሰላም አማራጮች ተፈፃሚ ይሆኑ ዘንድ አሉታዊ ሀሳቦችን ከሚያራምዱ አካላት መራቅ እንደሚኖርበትም ምሁራኑ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል፡፡

በዙፋን ካሳሁን