አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዳያስፖራው በሀገር ቤት የተፈጠሩ ዕድሎችን መጠቀምና ተሳትፎውንም ማጠናከር እንደሚገባው ተመላክቷል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በስዊዘርላንድ ከሚኖሩ የዳያስፖራ አባላት ጋር በጄኔቭ ባደረጉት ውይይት÷ ዳያስፖራው በሀገር ቤት የተፈጠሩ ዕድሎችን መጠቀምና ተሳትፎውን ማጠናከር እንደሚገባው አስገንዝበዋል።
የሚከሰቱ የውስጥ ግጭቶችን በሰላም ለመፍታት መንግስት እያከናወናቸው ያሉ ሥራዎችንም አብራርተዋል፡፡
የቆዩ የአለመግባባት ምንጭ የሆኑ ጉዳዮችን ለይቶ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ እየተከናወኑ ስላሉ ተግባራትም መናገራቸውን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
እንዲሁም የኢትዮጵያን የባሕር በርና ወደብ አጠቃቀም መብትን በተመለከተ ከዳያስፖራ አባላቱ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
የዳያስፖራ አባላቱም ወቅታዊ መረጃን ከሚመለከተው አካል በቀጥታ ለማግኘት የቻሉበት መድረክ በመመቻቸቱ መደሰታቸውን ገልጸው÷ ሀገራቸውን በሚችሉት ሁሉ ለማገዝ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!