አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢሲ) ”የባሕር በር የልማት በር” በሚል ርዕስ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት የፓናል ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዳምጠው ዳርዛ (ዶ/ር) በውይይቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ እንዴት ምላሽ ያግኝ በሚለው ጉዳይ ላይ ምሁራን አማራጭ ሐሳቦችን እንዲያቀርቡ ዩኒቨርሲቲ እየሠራ ነው ብለዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ከዚህ በፊት በነበሩ ወሳኝ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ አማራጭ ሐሳቦችን ማቅረቡን አስታውሰው፥ ለአብነትም የወሰንና የማንነት ጉዳይ፣ በሕገ-መንግሥት፣ በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንና በሌሎችም ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የበኩሉን መወጣቱን ጠቅሰዋል።
የወደብ ጥያቄ ዛሬ የጀመረ አለመሆኑን ጠቁመው፤ ቀደም ሲልም ሲነሳ መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡
በፓናል ውይይቱ ላይ÷ የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ከዓለም አቀፍ ሕግ አንጻር፣ የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ከጋራ ተጠቃሚነት አንጻር ምጣኔ ሐብታዊ ዕይታ፣ የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ አመክንዮዎች በሚል ርዕስ የውይይት መነሻ ጽሁፍ እየቀረበ ነው።
በተጨማሪም ተግዳሮቶች እና አማራጮች ከጂኦ ፖለቲካዊ እና ከውጭ ግንኙነት ዕይታ አንጻር እንዲሁም የውጭ ኃይሎች በቀይ ባሕር አካባቢ ያላቸው አዳዲስ ፍላጎቶች እና ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ያለው አንድምታ በሚል ርዕስ የመነሻ ጽሁፎች እየቀረቡ ይገኛሉ።
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በጥናትና ምርምር ላይ እንዲሠራ ተልዕኮ ከተሰጣቸው ስምንት ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ ነው፡፡
በምስክር ስናፍቅ
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!