አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተመራ የልዑካን ቡድን በቻይና ሱቿን ግዛት ቼንዱ ከተማ የተለያዩ ቦታዎችን ጎብኝቷል፡፡
ልዑኩ በጉብኝቱ የቻይና ከተሞች የተቀናጀ ልማት ጽንሰ ሐሳብን ተግባራዊ በማድረግ ገጠርን ከከተማ ጋር በማስተሳሰርና በተቀናጀ የልማት ስትራቴጂ የማልማት ሥራን ተመልክቷል፡፡
እንዲሁም የከተማ ግብርናን በማስፋፋት ረገድ በከተሞቻቸው የስራ ዕድል ከመፍጠር ባሻገር የግብርና ውጤቶችን ማትረፍረፍ የቻሉባቸውን ስራዎች መጎብኘቱን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
ልዑኩ ከጉብኝቱ በኢትዮጵያ የተጀመረውን የሌማት ትሩፋት በይበልጥ ማስፋት የሚቻልበትን ልምድ መቅሰሙም ነው የተገለጸው፡፡
በተጨማሪም የቻይና ከተሞች በጽዳትና ውበት እንዲሁም ከተሞች ለሰው ልጅ ተስማሚ፣ ለቱሪዝም መስሕብ፣ ለነዋሪዎች ምቹ መሆናቸውን ጨምሮ በአካባቢ ጥበቃ የሰሯቸውን የተሳኩ ስራዎች ልዑኩ መጎብኘቱ ተመላክቷል፡፡
የልዑካን ቡድኑ በቻይና የነበረውን የስራ ጉብኝት በማጠናቀቅ ወደ አዲስ አበባ ተመልሷል::
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!