የሀገር ውስጥ ዜና

በአማራ ክልል የሰላም ጥሪውን ተከትሎ 251 ታጣቂዎች ወደ ተዘጋጀላቸው ማዕከል ገቡ

By ዮሐንስ ደርበው

December 23, 2023

አዲስ አበባመ፣ ታኅሣስ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል መንግሥት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተከትሎ በጭስ ዓባይ፣ በወረታ እና በአዲስ ዘመን አካባቢዎች የነበሩ 251 ታጣቂዎች ወደ ተዘጋጀላቸው ማዕከል መግባታቸው ተገለጸ፡፡

የመንግስትን የሠላም ጥሪ የተቀበሉ ታጣቂዎች በአቅራቢያቸው ወደ ሚገኝ የመከላከያ ሠራዊት ቀርበው መሳሪያ ማስረከባቸውን የደንቢያ አካባቢ ኮማንድ ፖስት አባል ሌተናል ኮሎኔል አዛናው ነጋሽ ተናግረዋል።

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከምስራቅ ደንቢያ ወረዳ ቆላ ድባ ከተማና አካባቢው እንዲሁም ከሻውራ ወረዳ የመንግስትን የምኅረት ጥሪ ተከትሎ ታጣቂዎቹ ወደ ተዘጋጀላቸው የመሰብሰቢያ ስፍራ መግባታቸውንም ነው ያስታወቁት፡፡

ጥሪውን ተቀብላችሁ መምጣታችሁ ለሠላም ያላችሁን ፍላጎት ያመላክታል፤ ሌሎችም የእናንተን ፈለግ ተከትለው የቀረበላቸውን የሠላም ጥሪ ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ማለታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!