አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከንግዱ ማኅበረሰብ አባላት ጋር እየተወያዩ ነው፡፡
ውይይቱ “የዘመነ ንግድ ሥርዓት ለላቀ ገቢ ዕድገት” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን÷ በመድረኩ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በመድረኩ የዘርፉን አገልግሎት በማዘመን ለንግዱ ማህበረሰብ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር አስተዳደሩ ከወረዳ ጀምሮ ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር ውይይቶች እንዳካሄደ ተገልጿል፡፡