አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ293 የመንግሥት ትምህርት ቤቶች የምገባ መርሐ-ግብር ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን የሸገር ከተማ አሥተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡
የቢሮው ኃላፊ አቶ ፊራኪያ ካሣሁን እንደገለጹት÷ የ2016 የትምህርት ዘመን ከተጀመረ ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ ባለው የምገባ መርሐ-ግብር 140 ሺህ 531 ተማሪዎች ተጠቃሚ እየሆኑ ነው፡፡
ከምገባ መርሐ-ግብሩ ጋር በተያያዘም ከ2 ሺህ 800 ለሚልቁ ወጣቶችና እናቶች የሥራ ዕድል መፈጠሩን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል፡፡
በታሪክ አዱኛ
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!